የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ (9ኛ ሳምንት) ጨዋታዎች ነገ መካሄድ የሚጀምሩ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታ የሆነውን ደሴ ከተማ ከፌደራል ፖሊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ አምዳችን ተመልክተነዋል ።

ወደ ላይኛው የኢትዮጵያ ሊግ ወደሆነው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ አንደኛ ሆኖ ማጠናቀቅ መስፈርት በሆነበት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በዚህ ሳምንት ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን በርካታ ፉክክር እየታየበት ይገኛል። በዚህ ምድብ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ የሆነው ደሴ ከተማ ነገ የመጨረሻውን ጨዋታ የሚያከናውን ሲሆን ከአጀማመሩ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ቢችልም ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ነጥብ ነጥብ መጣሉ እና ሽንፈት ማስተናገዱ የመሪነት ቦታውን ቢያስረክብም ከመሪው ያለውን የ2 ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደሜዳ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ። ባለፉት የውድድር ዘመናት በመጀመሪያው ዙር የነበረበትን ክፍተት አሻሽሎ የጀመረው ደሴ ከተማ ጥሩ ነጥቦችን መሰብሰብ ቢችልም በርካታ ተጫዋቾች ጉዳት ማስተናገዳቸው ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማግኘት ከነበረበት 12 ነጥብ 4 ነጥብ ብቻ እንዲሰበስብ አድርጎታል። በተለይ ደግሞ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በኤሌክትሪክ እና በለገጣፎ ተከታታይ ሽንፈት ማስተናገዱ በመሪነት የሚቀጥልበትን እድል አሳጥቶታል ። በዘንድሮው የምድብ ሀ ውድድር ከፍተኛ ፉክክር ከመታየቱም በላይ የሊጉ መሪዎች በየሳምንቱ የሚቀያየርበት ሁኗል።ክለቡን ጥሩ መሻሻል እንዳሳይ ያደረጉት አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ ባለፈው ሳምንት ያጡትን ነጥብ ለማግኘት እና ከመሪዎቹ ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ቡድናቸውን እየመሩ ወደ ሜዳ ይገባሉ ።በጉዳት ምክንያት በርካታ ተጫዋቾችን ያጣው ደሴ ለነገው ጨዋታ የመድረሳቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ለቡድኑ ትልቅ ክፍተት ነው። ተጋባዡ ፌደራል ፖሊስ ባንፃሩ እስካሁን ካደረጋቸው 7 ጨዋታዎች በሶስቱ አሸንፎ በ 1 አቻ እና ሶስት ጊዜ ተሸንፏል ።በአንፃሩ ደሴ 4 አሸንፎ 2 ተሸንፏል ።የጎል ብዛት ስንመለከት ደሴ 9 አስቆጥሮ 4 የተቆጠረበት ሲሆን ፌደራል ፖሊስ 6አስቆጥሮ 8 ተቆጥሮበታል ። ደሴ 13 ነጥብ እና ፌደራል ፖሊስ 10 ነጥብ ይዘው በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ የሚገኙ ሲሆን ከመሪው መከላከያ ያላቸውን ነጥብ ለማጥበብ ይፋለማሉ ። በደሴ በኩል ቶስላች፣አንዋር ፣አብዱ እና አክዌር ለነገው ጨዋታ መሰለፋቸው አጠራጣሪ ነው።
ያለፉትን 3 ጨዋታዎች(ከቅርብ ወደ ሩቅ)
👉ደሴ –ተሸነፈ-ተሸነፈ-አሸነፈ
👉ፌደራል ፖሊስ-አቻ-ተሸነፈ-አሸነፈ
የእርስ በርስ ግንኙነቶች
-እስካሁን በሊጉ አምስት ጊዜ ተገናኝተው ደሴ አራት ጊዜ ፌደራል ፖሊስ ደግሞ አንድ ጊዜ በተመሳሳይ 1-0 አሸንፈዋል ።
-በድምሩ 5 ጎሎች ተቆጥረዋል ።
ግምታዊ አሰላለፍ
ደሴ ከተማ(4-3-3)
ሰለሞን-ሳሙኤል-በረከት-አስናቀ
ኤርምያስ -ዮሴፍ -በድሉ
ልዑልሰገድ -አቡበከር -ብርሃኑ